መልካም ዜና ለአፊኒ ሚዲያና እና ኮሙኒኬሽን ተከታታዮች
አፊኒ ሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ሐዋሳ
አፊኒ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን በሀገር ደረጃ በተለይ የሲዳማ ክልል ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፤ ፖለቲካዊ እንዲሁም በልዩ ልዩ ኹነቶችን ሽፋን በመስጠት በህትመት እና በዲጂታል አማራጭ መረጃዎችን ሲያደርስ፣ ዘገባዎችን ሲሰራ፣ ትንታኔ ሲሰጥ፣ በየዘርፉ የምሁራንን አስተያየት በማከል የህዝብን ጥቅም ማዕከል በማድረግ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በህትመት፡- በይዘትም በአቀራረብም ልዩ የሆነው አፊኒ መጽሄት የሲዳማን ባህል፣ ስነ-ጽሁፍ፣ ታሪክ፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስተዋወቅ በሶስት ቋንቋ ቃለ መጠየቆችን ጨምሮ ልዩ ልዩ አዝናኝና አስተማሪ ዝግጅቶችን ለተደራሲያኑ በማድረስ ውጤታማ ሥራ ሰርቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተላያዩ ኢቨንቶችን በማዘጋጀት፤ ቱር እና ትራቭል( Tour and travel) እንዲሁም ሀይኪንግ በማዘጋጀት ከክልል ደረጃም አልፎ በአዲስ አበባም ብዙ ደማቅ አሻራውን አሳርፏል።
በብዙ ፈተናዎች መካከል በመጽሄት ህትመት እስከ 7ኛ ዕትም የደረሰው አፊኒ ሚዲያ፣ በሀገር ደረጃ የግል ሚዲያ ኤዲቶሪያል ህጋችን በሚፈቅደው መንገድ ህብረተሰቡን ከማገልገል ጎን ለጎን ሀገር ለመገንባት በሚዲያ ዘርፍ በሚደረገው አስተዋፅኦ የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል። ለህብረተሰብ ሁለንተናዊ ልማት በተለይ በሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ የድርሻውን የመወጣት ዓላማን አንግቦ በህግ የተመሠረተው አፊኒ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን፣ ከስድስት ለተሻገሩ ዓመታት ወቅታዊ መረጃ፣ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ የዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የበኩሉን ከማበርከት ባሻገር የትምህርትና የሥራ ዕድሎችን መረጃዎችን በማጋራት ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
ከዚህ መነሻ ሚዲያችን የተደራሽነት አድማሱን በማስፋት፣ ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ስልትና ቴክኖሎጂ በመጠቀም እንዲሁም ለተመልካች፣ ለአድማጭና ለአንባቢያን ምቹ ሆኖ ለመቅረብ የአፊኒ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ድህረ-ገጽን (website :- www.affinimedia.com ን) ይፋ መሆኑን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው፡፡ ሚዲያችን በአዲሱ አማራጭ በተለያዩ ቋንቋዎች በፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚ እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሰፋ ያሉ ትንታኔዎች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዜጎችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ለማጎልበት የነጻ ሀሳብ አምድን፣ የድርጅቶችን እና የግለሰቦችን ምርትና አገልግሎትን ለማስተዋወቅ የማስታወቂያ አማራጭ ይዞ ቀርቧል፡፡ በመጨረሻም የአፊኒ መጽሔት የቀድሞ ዕትሞችን በማከል ሰፋ ያለ ይዘት ዌብሳይታችንን www.affinimedia.com ስራ መጀመራችንን እንገልጻለን።
በአዲሱ ይዘት በክልላችን ይሁን በሀገር ደረጃ የሚስተዋሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካ ነክ ፕሮግራሞች፥ በተሻለ አቀራረብ፣ በልዩ ሁኔታ የሚቀርቡበት ይሆናል።
ከአፊኒ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ጋር አብረው ይስሩ።
ለሁለንተናዊ ልማት የግልዎን ይወጡ።
ድህረ-ገጽ፡- www.affinimedia.com
AFFINI_PODCAST
አፊኒ_ሚዲያና_ኮሙኒኬሽን
ትኩስ እና እውነተኛ መረጃዎችን ለማግኘት ይከታተላሉ
ዩቲዩብ: https://youtube.com/@affinimediaofficial8818...
ቴሌግራም ፣ https://t.me/affinimedia
ትክቶከ ፣https://www.tiktok.com/@affinimediaoffici?_r=1...
ምንም ተዛማጅ ፅሁፎች አልተገኙም